Eshete Bekeleሰኞ፣ ሚያዝያ 21 2016በኬንያ ከመጋቢት ጀምሮ እየጣለ የሚገኘው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 76 አሻቀበ። ሱዳን በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች “ትንኮሳ” ላይ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በአስቸኳይ እንዲወያይ ጥያቄ አቀረበች። የፖርቹጋል መንግሥት አፍሪካውያን በባርነት ሲሸጡም ሆነ በቅኝ ግዛት ወቅት ለተፈጸሙ ወንጀሎች ካሳ ለመክፈል ምንም አይነት ሒደት እንደማይጀምር አስታወቀ። ወግ አጥባቂው የእስራኤል የፋይናንስ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች በራፋ የታቀደው ወረራ ከተሰረዘ የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁን መንግሥት እንደሚያፈርሱ ዛቱ። ሁለት ዩክሬናውያን በላይኛው ባቫሪያ በስለት ተወግተው መገደላቸውን የጀርመን ፖሊስ አስታወቀ።