1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሪታንያ የመጀመርያዉን ፈቃደኛ ስደተኛ ወደ ሩዋንዳ ላከች

ዓርብ፣ ሚያዝያ 25 2016

ብሪታንያ ፓርላማ ተቀባይነት ያላገኙ ጥገኝነት ጠያቄዎችን ለመመለስ መወሰኑን ተከትሎ፤ የመጀመርያዉ ፈቃደኛ ተመላሽ ወደ ሩዋንዳ መወሰዱ ታወቀ። ባለፈዉ ሰኞ በፈቃደኝነት ወደ ሩዋንዳ እንዲመለስ የተደረገዉ ስደተኛ መዲና ኪጋሊ መድረሱም ታዉቋል። ብሪታንያ ተቀባይነት ያላገኙ ተገን ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ የሚያስችላትን በሕግ ማጽደቋ ይታወቃል።

https://p.dw.com/p/4fTZk
ብሪታንያ ተቀባይነት ያላገኙ ተገንጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዉሳኔዋን የተቃወመ ሰልፍ በለንደን
ብሪታንያ ተቀባይነት ያላገኙ ተገንጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዉሳኔዋን የተቃወመ ሰልፍ በለንደን ምስል Niklas Halle'n/AFP/ Getty Images

ብሪታንያ የመጀመርያዉን ፈቃደኛ ስደተኛ ወደ ሩዋንዳ ላከች

ብሪታንያ ፓርላማ ተቀባይነት ያላገኙ ጥገኝነት ጠያቄዎችን ለመመለስ መወሰኑን ተከትሎ፤ የመጀመርያዉ ፈቃደኛ ተመላሽ ወደ ሩዋንዳ መወሰዱ ታወቀ። ባለፈዉ ሰኞ በፈቃደኝነት ወደ ሩዋንዳ እንዲመለስ የተደረገዉ ስደተኛ መዲና ኪጋሊ መድረሱም ታዉቋል። ብሪታንያ ተቀባይነት ያላገኙ ተገን ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ የሚያስችላትን በሕግ ባለፈዉ ሰሞን በሕግ ማጽደቋን ተከትሎ ነዉ።

የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪቺ ሱናክ ብሪታንያ የሚገኙ ተገን ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ከመላክ የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለ ማስታወac,ዉ ይታወሳል። ሱናክ ይህን ያሉት የብሪታንያ ፓርላማ ስደተኞች በትናንሽ ጀልባዎች ወደ ብሪታንያ እንዳይመጡ የሚከለክል ሕግ ካጸደቀ በኋላ ነው። በቅርብ ዓመታት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ የአፍሪቃ ፣መካከለኛው ምሥራቅና የእስያ ስደተኞች በሀገራቸው በሚደርሱባቸው የተለያዩ ችግሮች ምክንያት በሰዎች አሻጋሪዎች በኩል በትናንሽ ጀልባዎች የእንግሊዝ ቻናልን በማቋረጥ ወደ ብሪታንያ ገብተዋል።

 ሪቺ ሱናክ፤ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር
ሪቺ ሱናክ፤ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትርምስል Benjamin Cremel/Pool via REUTERS

ባለፉት ሁለት ዓመታት ብሪታንያ ፍልሰቱን ለማስቆም ከመካከላቸው አንዳንዶቹን ከሀገርዋ የማባረር ሙከራ ስታደርግ ቆይታለች።  ሕጉ በመጽደቅ መንግሥት ተገን ጠያቂዎችን ከዚህ ቀደም አቅዶ ወዳልተሳካለት ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዝግጅቱን በአንድ ፈቃደኛ ተመላሽ ስደተኛ ጀምሯል።  ሱናክ እንደተናገሩት ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ባለው ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያዎቹ የሩዋንዳ በረራዎች ይጀመራሉ ብለዉ ነበር። 500 ሰራተኞች፣ ተገን ጠያቂዎቹን አጅበው ለመውሰድ መዘጋጀታቸዉም ገልፀዉ ነበር። ፍርድ ቤቶችም አቤቱታዎችን ለማስተናገድ እየጠበቁ መሆናቸዉም አክለዉ ነበር።  ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ማባረርን  ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ሲቃወሙት ቆይተዋል። ተችዎች እቅዱን ኢሰብዓዊ እርምጃ ይሉታል።

 

መኮንን ሚካኤል

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ