1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ቆርቃ ቀበሌ ነዋሪዎች ቅሬታ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 25 2016

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ቆርቃ ቀበሌ ውስጥ ባለፈው ማክሰኞና ረቡዕ ከ30 በላይ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ነዋሪዎች እንደሚሉት ጥቃት አድራሾቹ ከዚህ በፊት በጉሙዝ ህዝብ ንቅናቄ ስም ይንቀሳቀሱ የነበሩ እና በአሁኑ ወቅት ከሰላም ስምምነት በኃላ የሰላም ተመላሽ የተባሉ ታጣቂዎችና ሚሊሻዎችም መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4fUL6
አሶሳ ከተማ
አሶሳ ከተማ ምስል Negassa Desalegn/DW

የመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ቆርቃ ቀበሌ ነዋሪዎች ቅሬታ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ቆርቃ የሚባል ቀበሌ ውስጥ ባለፈው ማክሰኞና ረቡዕ ከ30 በላይ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ነዋሪዎች እንደሚሉት ጥቃት አድራሾቹ ከዚህ በፊት በጉሙዝ ህዝብ ንቅናቄ ስም ይንቀሳቀሱ የነበሩ እና በአሁኑ ወቅት ከሰላም ስምምነት በኃላ የሰላም ተመላሽ የተባሉ ታጣቂዎችና ሚሊሻዎችም መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ጥቃቱ ማንነት ላይ ያተኮረና በአንድ የቆርቃ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ማሳ ውስጥ የወርቅ ክምችት መገኘቱን ተከትሎ ታጣቂዎቹ አርሶ አደሮችንን ከአካባቢው ለማባረር ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የዞኑ አስተዳደር ስለጉዳዩ መረጃ የለምኝ ብሏል፡፡

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ቆርቃ የተባለ ቀበሌ ማክሰኞ ዕለት መኖርያ ቤታቸው መቃጠሉን የነገሩን ነዋሪ በአሁኑ ወቅት እሳቸውን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ወደ ጫካ ሸሽተው እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በሁለት አቅጣጫ ወደ አካባው በመዝቀለቅ በሠላማዊ ሰዎች ላይ ተከስ በመክፈት በቀበሌው መኖርያ ቤቶችን መቃጠላቸውን ገልጸው ለዚህ ጥቃትም በአካባቢው ባለፈው ዓመት በጉምዝ ህዝብ ንቅናቄ(ጉህዴን) ስም ታጥቆ ይንቀሳቀሱ የነበሩ በአሁኑ ወቅት የሰላም ተመላሽ ተብሎ የሚጠሩና የአካባቢው ጸጥታ ሐይል ተጠያቂ አድርጓል፡፡ በአካባቢው ወርቅ መገኘቱን ተከትሎ ማክሰኞ ግጭት መቀስቀሱንና በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ መከፈቱን ተናግረዋል፡፡

በአካባቢው በተከሰተው የጸጥታ ችግር ቤታቸው መቃጠሉን እና ወደ ሌላ ቦታ መሸሻቸውን የነገሩን ሌላው ነዋሪም የእሳቸውን ጨምሮ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው የተገኘውን ወርቅ ማውጣት አልፈቀደላችሁም በማለት ከሽፋታ ጋር ግንኙነት አላችሁ የሚል ምክንያትበመፍጠር በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸው አመልክተዋል፡፡ እዛው ቆርታ የተባለ ቦታ አቅራቢያ በሚገኘው ጋለሳ ከተባለ ቀበሌም በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ከአምስት በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ገልጸዋል፡፡

‹‹ ቆርቃ ቀበሌ ላይ ብዙ ቤት ነው የተቃጠለው፡፡ ወርቅ የተገኘው በግለሰብ ማሳ ውስጥ ነው፡፡ በግለሰቡ መኖርያ በቅርብ ርቀት ላይ ነው፡፡ በዚሁ ምክንያት ብሔርን ምክንያት በማድረግ መኖርያ ቤቶችን በማቃጠል ሰዎችን ከቦታው አባረሩ፡፡ አንድ ወጣት ደግሞ በአንድ ወንዝ አቅራቢያ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ አልፈዋል፡፡››

በድባጢ ወረዳ ቆርቃና ጋለሳ አካባቢ የተነሳቸው የነዋሪዎችን ቅሬታ አስልመክቶ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ለሜሳ ዋወያ የተቃጠለ ቤት የለም ብሏል፡፡ በአካባቢው ስላለው ጉዳይም መረጃ እንደለላቸው ተናግረዋል፡፡

መተከል ዞን ከዚህ ደቀም በነበረው የጸጥታ ችግር ለረጅም ጊዜ በኮማንድ ፖስት ሲጠበቅ የነበረ አካባቢ ሲሆንን ከዞኑ ተፈቅለው ወደ ሌላ አካባቢ ሸሽቶ የነበሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም ወደ አካባቢአቸው መመለሱን የክልሉ መንግስት ገልጸዋል፡፡ በዲባጢ ወረዳ ጋለሳና ቆርቃ የተባሉ አካባቢዎች ለረጅም ወራት ሰላም ሰፍኖ እንነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ