1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመኖሪያ ቤት እጥረትና የቤት ክራይ ውድነትን ለመቀነስ ያስችላል የተባለ አዋጅ ፀደቀ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 25 2016

ከግዜ ወደግዜ እየናረ የመጣውን የመኖሪያ ቤት እጥረት እና የቤት ክራይ ውድነትን ለመቀነስ ያስችላል የተባለ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆዋል። አዲሱ አዋጅ እስካሁን የቤት ክራይ ዋጋን በተመለከተ ፍላጭ ቆራጭ ናቸው የሚባሉትን የመኖሪያ ቤት አከራዩች እንዳሻቸው ዋጋ ከመጨመር ያግዳቸዋል ።

https://p.dw.com/p/4fU79
የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምስል Yohannes Gebireegziabher/DW

የመኖሪያ ቤት እጥረት እና የቤት ክራይ ውድነትን ለመቀነስ ያስችላል የተባለ አዋጅ ፀደቀ

የመኖሪያ ቤት እጥረት እና የቤት ክራይ ውድነትን ለመቀነስ ያስችላል የተባለ አዋጅ ፀደቀ

ከግዜ ወደግዜ እየናረ የመጣውን የመኖሪያ ቤት እጥረት እና የቤት ክራይ ውድነትን ለመቀነስ ያስችላል የተባለ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅድቆዋል ምክር ቤቱ ያፅደቀው አዋጅ አዋጅ ቁጥር 1320/2016 የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርን እና አስተዳደር ይመለከታል 

ይህ አዋጅ ቀደም ብሎ በቃል እና በእምነት በተከራይ እና አከራይ መካከል   ይደረግ የነበረው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል  በአዲሱ አዋጅ አንቀፅ 4 መሰረት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል በፅሁፍ ማድረግን  ግዴታ ከማድረጉም ባሻገር  ውሉ በተቆጣጣሪው አካል ተረጋግጦ እንዲመዘገብ ያዛል  ግዴታቸውን ያልተወጡ አከራይና ተከራይ ላይ  የቤት ክራዪን የሦስት ወር ገንዘብ  ቅጣት  አዋጁ አስቀምጧል። ከዚህ ቀደም  ተከራይ   የሶስት  እና የስድስት ወር ቅድሚያ ክፍያ ለአከራይ መስጠት ግዴታው የነበረ ሲሆን  በአዲሱ አዋጅ  ግን  ተከራይ የሚጠበበት  የሁለት ወር  ኪራይ ቅድመ ክፍያ   ብቻ  ነው ።

ክፍያውም በባንክ ወይም በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ መፈፀም ይኖርበታል ይህ አስገዳጅ ህግ አዲስ የሚፈስም የኪራይ ውል ብቻ ሳይሆን እድሳትንምያካትታል ፣ በአዲሱ አዋጅ አንድ የምኖሪያ ቤት ክራይ ውል  የቆይታ ጊዜ ሁለት ዓመት ነው ። በዚህ ግዜ ውስጥ አከራይ  ተቆጣጣሪው ከሚያወጣው የክራይ ጣሪያ ውጭ ምንም እይነት የቤት ክራይ ጭማሪ ማድረግ አይችልም። 

አዲሱ አዋጅ እስካሁን የቤት ክራይ ዋጋን በተመለከተ ፍላጭ ቆራጭ ናቸው የሚባሉትን የመኖሪያ ቤት  አከራዩች  እንዳሻቸው ዋጋ  ከመጨመር ያግዳቸዋል ።   አቅምን ያማከል የመኖሪያ ቤት እጥረት  ችግር  ሳቢያ የሚፈጥዕረውን  የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ አይነተኛ መፍትሄ  ነው ተብሎዋል  ። DW ያናገራቸው የአዲስ አበባ የቤት ክራይ ነዋሪዎች ስጋታቸውን እንዲህ ይናገራሉ አዲስ ቤት ለኪራይ የሚያቀርቡ አከራዮችን የመጀመሪያውን የቤት ኪራይ ውል ካስመዘገቡበት ቀን ጀምሮ በአዋጁ መሰረት ከሚወጡ የኪራይ ዋጋ ጣሪያ ግዴታዎች ለአራት አመት ነፃ ይኾናሉ የሚል የማበረታቻ ሲኖረው በሌል በኩል ባለቤቶች  ቀደም ብሎ ሲከራይ የነበረን ቤት ከስድስት ወር በላይ ሳይከራይ እንዲቆይ ቢያደርጉ ቤቱ ቢከራይ  ያስገኝ የነበረውን የቤት ኪራይ ግብር ገቢ ታስቦ በማግረግ እንዲከፍሉ ይደረጋል  ይላል ።

የህግ ባለሙያው አቶ ካፒታል ክብሪ ለ DW እንደተናገሩት አዋጁ በ ግለሰቦች ለፍተው ባፈሩት ሀብት ላይ የሚኖራቸውን መብት ለመገደቡ አሻሚ አይደለም ይላሉ

ትክክለኛው መፍትሄ ኢኮኖሚያዊ ላይ መስራት ነው ። እንደውም  በጣም ጥብቅ የሆነ ህግ በውጣቁጥር  የበለጠ አልሚዎችን በመጉዳት ችግሩን  ከድጡ ወደማጡ ሊወስደው ይችላል ይላሉ

ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት እጥረት ባለባቸው ከተሞች የመኖሪያ ቤትን አላግባብ ከህግ ውጭ አገልግሎት ሳይሰጡ ከአንድ አመት በላይ ለሚያቆዪ ባለንብረቶች ከኪራይ ግብር በተጨመሪ የቤቱን ንብረት ግምት ተምን 25 ክርመቶ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ መመሪያ እንዲያወጡ  አዋጁ ለየከተሞች መብት ሰጥቶዋል

ሃና ደምሴ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ