1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

“የቡና መገኛ ስፍራ”ን የማልማት ጥያቄ

ቅዳሜ፣ ጥር 18 2016

ጅማ ዞን ጎማ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው እና በቡና መገኛነት የተያዘው “ከታ ሙዱገጋ (ጮጬ)” የሚባል ስፍራ እንዲለማ እና የቱሪስት መስዕብ ብሎም የምርምር ማዕከል እንዲሆን ተብሎ እንቅስቃሴው ቢጀመርም ቦታው አለመልማቱ በአከባቢው ማህበረሰብ ቅሬታ ያስነሳል፡፡

https://p.dw.com/p/4bkQG
Äthiopien | Kaffee
ምስል Seyoum Getu/DW

የቡና ሙዚየም በተያዘለት ጊዜ አልተገነባም ፤ ነዋሪዎች

በጅማ ዞን  ጎማ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው እና  በቡና መገኛነት የተያዘው “ከታ ሙዱገጋ (ጮጬ)” የሚባል ስፍራ እንዲለማ እና የቱሪስት መስዕብ ብሎም የምርምር ማዕከል እንዲሆን ተብሎ እንቅስቃሴው ቢጀመርም ቦታው አለመልማቱ በአከባቢው ማህበረሰብ ቅሬታ ያስነሳል፡፡

እንደ የአከባቢው ማህበረሰብ አስተያየት ቦታውን ለማልማል 17 ዓመታት የፈጀ ሃሳብ ብኖርም እስካሁን ይህ ነው የሚባል ስራ አለመሰራቱንም ነው የሚገልጹት፡፡

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ጎማ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው በጅማ የቡና መገኛ ነው የሚባልለት ጮጬ (ከታ ሙዱጋ) ከጅማ ከተማ 45 ኪ.ሜ ገደማ ላይ ከምትገኘው አጋሮ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ይህ ስፍራ የአረቢካ ቡና መገኛ ነው በሚል በአካባቢው የአገር ሽማግሌዎች ይነገራል፡፡

ይህቺ ከታ ሙዱጋ በመባል የምትታወቀውና በታሪካዊ ቅርስነት የተያዘችው ስፍራ በቡና እና ሌሎችም ደኖች ተከባ በመሃል ላይ የተወሰነውን አካባቢ አለታማ ድንጋይ  ይሸፍናታል፡፡ አህመድ አባገሮ በጎማ ወረዳ አባገዳ እና የአከባቢው ታሪክ አዋቂ የአገር ሽማግሌ ናቸው፡፡ “ይህቺ ስፍራ ከደን የተከበበች አለት ናት” ይላሉ፡፡የአውሮፓ ኅብረት የደን ጭፍጨፋ ለመግታት ያወጣው ሕግ የኢትዮጵያ ቡና ገበሬዎች እና ላኪዎችን ሥጋት ላይ ጥሏል

የአገር ሽማግሌው አህመድ አባገሮ ይህ ስፍራ የቡና መገኛ የተባለበትን ምክኒያት ሲያስረዱም፤ “ሀረግ የተጠመጠመበትን ቀልቶ ለውን ቡና ፍየል በልቶ ሲመረቅን የተመለከቱት እግዶች ካሊድ ከተባለው እረኛ ከተረዱ በኋላ ቡናውን ለቀመው በቆሉ ጊዜ የቡናውን ጥቅም በቨመረዳታቸው ችግኙን አስፋፍተው ምርቱንም ለገቢ አዋሉት” ይላሉ፡፡ ከዚም በአረብ ስፖንሰር አድራጊነት ጀርመኖች ስፍራውን አትንተው ቦታውም የአረቢካ ቡና መገኛ ተሰኘ ሲሉ ሃሳባቸውን አስረዱ፡፡

ጮጬ ከታ ሙዱጋ
በኢትዮጵያ ውስጥ በቡና መገኛነት ስፍራ የተለያዩ ውዝግቦች እንደሚነሱ ይታወቃል፡፡ በተለይም የቡና መገኛ ከፋ ነው በሚል በተለያዩ ጊዜያት ሃሳቦችም ተንጸባርቀዋል፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

ይሁንና በኢትዮጵያ ውስጥ በቡና መገኛነት ስፍራ የተለያዩ ውዝግቦች እንደሚነሱ ይታወቃል፡፡ በተለይም የቡና መገኛ ከፋ ነው በሚል በተለያዩ ጊዜያት ሃሳቦችም ተንጸባርቀዋል፡፡ ስለዚሁ ጉዳይም የተጠየቁት አህመድ አባገሮ ይህ አከባቢ ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ የከፋ ክፍላገር ተብሎ ብተዳደርም ቡናው በተገኘበት በ13ኛ መቶ ክፍለ ዘመን አከባው በገዳ ስርዓት በታሪካዊው የጅማ አከባቢ ነገስታት ይተዳደር እንደነበር አስተያየታቸውን አከሉ፡፡ “ይህ ቦታ የቡና መገኛነቱ ከተረጋገጠ ከ500 ዓመታት በኋላ ነው አጼ ሚኒሊክ 30 ሺህ ሰራዊት ከፋ አምጥተው ለራስ ወልደጎዮርጊስ እንዲያስተዳድሩ ሲሰጡት አስተዳዳሪው  ከፋ ያንሰኛል ሲሉ በ1992 ዓ.ም. ጅማንም ጨምረው ከፋ ክፍለ አገር በሚል እንዲያስተዳድሩ ተሰጣቸው፡፡”

ጮጬ ከታ ሙዱጋ
ይህ ቦታ የቡና መገኛነቱ ከተረጋገጠ ከ500 ዓመታት በኋላ ነው አጼ ሚኒሊክ 30 ሺህ ሰራዊት ከፋ አምጥተው ለራስ ወልደጎዮርጊስ እንዲያስተዳድሩ ሲሰጡት አስተዳዳሪው  ከፋ ያንሰኛል ሲሉ በ1992 ዓ.ም. ጅማንም ጨምረው ከፋ ክፍለ አገር በሚል እንዲያስተዳድሩ ተሰጣቸው፡፡”ምስል Seyoum Getu/DW

የሆነ ሆኖ ይህ ስፍራ የታሪክ ቦታነቱ ከተረጋገጠ በኋላ ስፍራው እንዲለማና የቱሪስቶች መዳረሻም እንዲሆን በሚል እቅስቃሴ ይጀመራል፡፡ የአከባቢው የአገር ሽማግሌው እንደሚሉት በተለይም በ1999 ዓ.ም. የወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩ አቶ አባዱላ ገመዳ ቦታው ላይ መሰረተ ድንጋይ ብያስቀምጡም፤ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስም ቦታውን ብጎበኙም እስካሁን ይህ ስፍራ ተፈላጊውን ልማት እንዳላገኘ የአከባቢው ማህበረሰብ ላይ ቅሬታን ፈጥሯል፡፡የትስስር የቡና ንግድ መንገዱ አቋራጭ ወይስ? በዚህ ስፍራ አሁን ላይ የቡና መጠጫ ከተባለች አንዲት ጎጆና የዘበኛ ቤት ውጪ የሚታይ የመንገድም ሆነ ምንም አይነት ልማት አይስተዋልበትም፡፡ “ይህን ሁሉ ታሪክ ተሸክመን ከጫካው ጋር እንዲሁ ስንኖር እራሳችን የምንመለከተው እንደታገተ ሰው ነው” ላሉ አህመድ አባገሮ፡፡ ቦታው ለምቶ በጉልህ እንዲተዋወቅም ጥሪያቸውን አሰምተዋል፡፡

ጮጬ ከታ ሙዱጋ
በዚህ ስፍራ አሁን ላይ የቡና መጠጫ ከተባለች አንዲት ጎጆና የዘበኛ ቤት ውጪ የሚታይ የመንገድም ሆነ ምንም አይነት ልማት አይስተዋልበትም፡፡ “ይህን ሁሉ ታሪክ ተሸክመን ከጫካው ጋር እንዲሁ ስንኖር እራሳችን የምንመለከተው እንደታገተ ሰው ነው” ላሉ አህመድ አባገሮ፡፡ ምስል Seyoum Getu/DW

ይህ ሃሳብ በርካታ የአከባቢውን ነዋሪዎች ያስማማል፡፡ በጅማ በታሪክ አዋቅነታቸው የሚታወቁት አብዱልከሪም አባገሮም ሃሳቡን ተጋርተው አስተያየታቸውን ያከሉት በቁጭትም ጭምር ነው፡፡ “ከታ ሙዱጋ የቡና መገኛ ስፍራ እንደመሆኑ በዚያ ስፍራ ሙዚየም ተሰርቶ የቡና ምርምር ብካሄድበት መልካም ነው” በማለት ሃሳባቸውን ገልጸዋል፡፡      

ሥዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ